የጨረታ ማስታወቂያ
በኢሉባቦር ዞን የአሌ ወረዳ ገ/ኢኮ/ት/ጽ/ቤት በ2013 በጀት አመት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች እና ለቴክኒከና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ የሚሆን ፡
- የጽህፈት መሣሪያዎች ፤
- አላቂ እቃዎች፤
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- የፈርኒቸርና የቢሮ እቃዎች፤
- የግንባታ ዕቃዎች
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤
- የመኪናና የሞተር ሳይክል ጎማና ካለመዳሪያ
- የስፖርት ትጥቅ የልብስ ማሰፊያ የእጅ ዋጋ
ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ለሚያሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- በአቅራቢዎች መዝገብ ላይ ስለመመዝገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የቲን ቁጥር ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እና ተጫራቹ በሚያቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 5000(አምስት ሺህ) በካሽ ማስያዝ የሚችል
- አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃዎች እስከ አሌ ወረዳ ገን/ኢኮ/ት/ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ውል ማስከበሪያ ባሸነፉበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በካሽ ማስያዝ የሚችል
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሰለሆነ ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ከአሌ ወ/ገን/ኢኮ/ት/ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች የማወዳደሪያ የዕቃ ሙሉ ስምና ዋጋ የተሰራበት ሀገርና የጥራት ደረጃውን አሟልተው እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የዕቃውን ናሙና ማቅረብ አለባቸው
- ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአሌ ወ/ገን/ኢኮ/ት/ጽ/ቤት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ ኦሪጅናሉንና ፎቶኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ይህ ማስታወቂያ ከዚህ በፊት በወረዳው ላይ ተወዳድሮ ካሸነፉ በኋላ በውሉ መሠረት ያላቀረቡት ተወዳዳሪዎች አይመለከትም።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– አሌ ወረዳ ገ/ኢኮ/ት/ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር 04755 40066/0475540891/0475540390
በኢሉባቦር ዞን የአሌ ወረዳ ገ/ኢኮ/ት/ጽ/ቤት