ግልጽ የጨረታ ማስታዎቂያ
የአለፋ ወረዳ ፍ/ቤት የ2013 ዓ.ም የተለያዩ ጥቅል ግዥ በግልጽ ጨረታ በማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጯራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ሎት1 ስቴሽነሪ(የጽህፈት መሣሪያ)፣ሎት2 የጽዳት ዕቃዎች ፣ ሎት3 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ፣ሎት4 የህትመት ዕቃዎች ፣ሎት5 የደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶች፣የቆዳ ጫማ፣ ፕላስቲክ ቦት ጫማ፤ጥላ ፣ሎት6 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፈቃድ ያለዉ
- በ2013 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው
- የግዥ መጠን 50 ሽህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጯራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻችን ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጯራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመልስ ብር 20.00/ሃያ ብር/ ብቻ በመክፈል በባህርዳር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ዋ/የስ ቡድን ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጯራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋጋውን የሚወዳደሩበት ብር 1 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ሲ.ኘ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጯራቾች ከእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናሉም ሆነ ኮፒው ላይ መፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸዉ፡፡
- ተጯራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያው ጋር በማድረግ በስም በታሸገ ፖስታ በባህርዳር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ዋ/የስ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ከህዳር 21/03/2013 ዓ.ም እስከ 05/04/2013 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸል፡፡የጨረታ ሳጥኑ ህዳር 06/04/2013 ዓ.ም ከጥዋቱ 2፡30 ይታሸጋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከኦርጅናሉ የጨረታ ሰነድ ጋር መታሸግ አለበት፡፡
- ጨረታው ተጯራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችን በተገኙበት በባህርዳር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ዋ/ የስ ቡድን ቢሮ ህዳር 06/04/2013 ዓ.ም በ3፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ክብ ማህተም ማድረግ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
- የጨረታዉን ሰነድ ሲገዙ ዉድድሩ በጥቅል ወይም (በሎት) ስለሆነ ሁሉም መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ ካልሞሉ ከዉድድር ዉጭ ይሆናሉ፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም
- በስልክ ቁጥር 0918467084 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ መ/ቤቱ በሎትም ሆነ በነጠላ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአለፋ ወረዳ ፍ/ቤት