የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ በደቡብ ኦሞ ዞን የኛንጋቶም ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመደበኛካፒታል በጀት የካንጋቴን ከተማ የመናኸርያ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ
- የፋብሪካ ውጤቶች እና
- የእንስሳት መድኃኒት ግዥ ለመፈፀም በየዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት፦
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
- የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከኛ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ክፍል የማይመለስ ብር 100 አንድ መቶ ብር ብቻ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል የመጫረቻ ሠነዱን በመውሰድ በጨረታው መወዳደር ይችላል።
- ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ለፋብሪካ ውጤቶች 10,000/ አስር ሺህ ብር/ ሲሆን ለእንስሳት መድኃኒት 5,000 /አምስት ሺህ ብር በቻ/ ከታወቀ ባንክ በሲፒኦ ብቻ በማዘጋጀት ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ ከጨረታው ፋይናንሻል ኦርጅናል ዶክመንት ጋር በማስገባት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተገዛውን የጨረታ ሠነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ በአግባቡ በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በ16ኛው /አስራ ስድስተኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 እስከ 4:30 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል።ጨረታው በዚሁ ዕለት 4:35 ሰዓት ታሽጎ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 16ተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 09 16 83 23 13 ወይም 09 26 41 30 11
በደቡብ ኦሞ ዞን የኛንጋቶም
ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት