የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት የአቶ አይታ መሀመድ ተወካይ መሬም አይታ እና በፍ/ ባለዕዳ ወ/ት ራሔል ልዑልሰገድ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 70450 በ26/11/2011 ዓ.ም እና በመ/ቁ 72450 በ24/3/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤቁ.375/2 ቁጥር 4 የሚገኝ ንብረት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 81,268.00 (ሰማኒያ አንድ ሺ ሁለት መቶ ስልሳ ስምንት ብር ) ሆኖ ታኅሣሥ 2 ቀን 2013 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ ለሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን ፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
በተጨማሪ ተጫራቾች የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጉድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም
ዳይሬክቶሬት