የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የሚገኘው ነፃነት ብርሃን አፀደ ህፃናት የመጀ/ደ/ት ቤት ለ2013 የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉ ዕቃዎች ማለትም
- የደንብ ልብስ
- የስፖርት ትጥቅና ማቴሪያሎች
- ፕላንትና ማሽነሪዎች
- የጽዳት ዕቃዎች
- ፈርኒቸሮች
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የመሳሰሉትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ
- ለሚጫረቱበት ዕቃዎች በዘርፉ የንግድ ስራ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ፤ በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው ፤ የዘመኑ ግብር የከፈሉ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁTir /ቲን ነምበር/ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ኦርጅናሉን ከኮፒው ጋር በማመሳከር ኮፒውን ለብቻ ኦርጅናሉን ከጨረታ ሰነዱና ሲፒኦ ጋር በማያያዝ ማስገባት አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበርያ ሰነድ /ቢድ ቦንድ/ የኢትዮጵያ ብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር / በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ /ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከፋይናንስ ቢሮ ቁTir 20 የማይመለስ ብር 50 በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላትና በማሸግ ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራች ለሚጫረቱበት ዕቃ ጨረታውን ሲያስገቡ ናሙና /ሳምፕል/ አብረው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የአንዱን ዕቃ ዋጋ ሲያቀርቡ የቫትን ዋጋ ጨምረው ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ፤ በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሠዓት ይታሸግና በሚቀጥለው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ሠዓት ይከፈታል።
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ከደንበል ሲቲ ሴንተር ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ ድሪም ላይነር ሆቴል ገባ ብሎ ነው ።
ስልክ ቁTir ፡-011470-03-71 ወይም 0114-166514
በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ነፃነት ብርሃን አፀደ ህፃናት የመጀ/ደ/ት ቤት