Building and Finishing Materials / Construction Machinery and Equipment

የነጆ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴከተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

የነጆ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት 2013 . በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴከተር /ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው የሚገልጽ ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት በነጆ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት ቀርባችሁ መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡

 1. ተጫራቾች የታደሰና ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከሚመለከተው /ቤት የተመዘገቡበትን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋብ የሆኑ፤
 2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ብር 7000 (ሰባት ሺህ) ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
 3. የጨረታ ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን ጨረታ የቴክኒክ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን የፋይናንስ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት 230 እስከ 1130 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጋር መሆኑን መግለጽ አለባቸው፡፡
 5. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21ኛው ቀን 500 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በነጆ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር /ቤት አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል:: ሆኖም ቀኑ በዓል ወይም የእረፍት ቀን ላይ ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ሁኔታ ታሽጎ ይከፈታል።
 6. ለጨረታው ማስረከቢያ የተያዘ CPO ተመላሽ የሚሆነው አሸናፊ ድርጅት ከተገለጸ በኋላ ይሆናል::
 7. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሠረት የጨረታው አሸናፊነቱ በጽሑፍ እንደተገለጸ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ ገንዘብ 10% በማስያዝ በነጆ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት መጥተው ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ የጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው CPO ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
 8. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸው ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት በነጆ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 9. ማንኛውም ተጫራቾች ያለበቂ ምክንያት የተዋዋለውን ውል ካፈረሰ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በቅጣት መልክ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
 10. ይህን ጨረታ የሚጫረቱ ድርጅቶች የራሳቸውን እስቶር (መጋዘን) መኖር አለባቸው፡፡
 11. በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምሥክር ወረቀት ያላቸው ተጫራች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
 12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
 13.  ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስም እና የተመረተበትን ሀገር መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
 14. ተጫራች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡ ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ካቀረቡ ይዘው ይመለሳሉ፡፡
 15.  የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው ዝርዝር መሠረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውም ስህተት ሲፈጸም ሀላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል፡፡
 16. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቼአለሁ ማለት አይችልም፡፡
 17. /ቤታችን የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይቻላል፡፡
 18. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸው ዕቃዎች ጭነው ለማቅረብ ከጽሕፈት ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማሉ ሁሉ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ በጀት ዓመት መጨረሻ የሚቆይ ይሆናል፡፡
 19.  ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡
 20.  የዕቃዎችን ዋጋ የምንከፍለው ዕቃዎቹ በግምጃ ቤታችን ገቢ ከሆኑ በኋላ ነው፡፡ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከሥር በምንረከበው ዕቃ መጠን ወይም ብዛት ልክ ክፍያ መፈጸም ይቻላል፡፡
 21. በወቅቱ ያልቀረበ የጨረታ ሰነድ ከጨረታ ሳጥን ውጪ የተገኘ የጨረታ ሰነድ የባለቤትነት ወይም የህጋዊ ተወካይ ማስረጃ የሌለው ተጫራች ተቀባይነት የለውም፡፡
 22. በጨረታ ሰነድ ውስጥ ያልተቀመጠ መስፈርት ለግምገማ አያገለግልም፡፡ ጨረታው ሲከፈት ሁከት ማንሳት የተከለከለ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡በስልክ ቁጥር 0577740013/ 0577740108 እና 0917817733 ወይም 0913554324


n