ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የቻ/ከ/አስ/ገ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ እና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በተያዘው በጀት አመት ማለትም 2013 ለቻግኒ ከተማ አስተዳደር ለሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ማለትም
- ሎት 1 አላቂ እቃዎች
- ሎት 2 ሌሎች አላቂ (የጽዳት) እቃዎች
- ሎት 3 ቋሚ አላቂ እቃዎች፤
- ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤
- ሎት 5 የመብራት እቃዎች፤
- ሎት 6 ኢምፖርትድ ፈርኒቸር፤
- ሎት 7 የደንብ ልብስ፤
- ሎት 8 የህንጻ መሳሪያዎች፤
- ሎት 9 የስፖርት እቃዎች /አልባሳት/
- ሎት 10 አጋዥ ጋይድ እና የተለያዩ መጽሐፍት
- ሎት 11 የእንስሳት ቤተ-ሙከራ እቃዎች በበኩር ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መጫረት ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ያላችው፡፡
- ግዥው ከ200,000.00/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ/በመክፈል ከቻ/ከ/አስ/ገ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ እና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በመግዛት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በጽ/ቤታችን መሂ-1 ገቢ የተደረገበትን ኮፒ የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በፖስታው በማሸግ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች አሸናፊ ተለይቶ ውል ከተያዘ በኋላ ባሉት 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ በራሱ ወጭ እስከ የቻ/ከ/አስ/ገ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ እና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ድረስ አምጥቶ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግዥ እና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቻ/ከ/አስ/ገ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ እና ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ጨረታው በወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ይህ ቀን ብሔራዊ በአል ወይም እሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ በመፈረም የድርጅቱን ማህተም እና አድራሻ አድርጎ መመለስ አለበት
- ተጫራቾች ለግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊ የምንለየው በሎት በተሞላው ጥቅል ድምር ዋጋ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቻ/ከ/አስ/ገ/አ/ኢ/ል/ትብ/ጽ/ቤት ግዥ እና ፋይ/ንብ/አስ/ቡደን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582251721፣ 0582251631 በመደወል መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡
የቻግኒ ከተማ አስተዳደር ገ/አ/ኢ/ል/ጽ/ቤት