የጨረታ ማስታወቂያ
የትራንስፖርት ሚኒስቴር በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ
- የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎትና
- የመኪና ጥገና አገልግሎት ግዥ
በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በማወዳደር ውል በመዋዋል አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፤ ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ሚኒስቴር መ/ቤቱ 4ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል ፡፡
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው
- በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ንግድ ፍቃዳቸው የታደሰ መሆን አለበት
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ
- የግብር ከፋይ ቁጥር ያላቸው /TIN NUMBER/ ማቅረብ የሚችሉ
- የግዥው መጠን ብር 100000/አንድ መቶ ሺህ/በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ሰነድ ለእያንዳንዱ ጨረታ የማይመለስ ብር 100 (ብር አንድ መቶ) በትራንስፖርት ሚኒስቴር ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000000984365 ገቢ እያደረጋችሁ እስከ 15 ኛው የስራ ቀን ድረስ 4ኛ ፎቅ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የቴክኒክ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የተለያየ የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታበማድረግ እስከ 16ኛው የስራ ቀን 4፡00ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ
- በ16ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓትተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 604ይከፈታል
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር አስር ሺህ ብር 10000/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው ።
- ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ዋናው ፖስታ ቤት ትራንስፖርት ሚኒስትር ቢሮ 4ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 0115540265
የትራንስፖርት ሚኒስቴር