የተለያዩ የእንጨት ግብዓቶች፣ የኮላ እና ቀለሞች፤ የፈርኒቸር መገጣጠሚያ እና ማጠናቀቂያ እቃዎች ግዥ የሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ቁጥር ት.መ.ማ.ማ.ድ/NCB/02/2012
ድርጅታችን ለፈርኒቸር ምርት ግብዓቶችን በተለያዩ ሎቶች ከፋፍሎ ለመግዛት ብቃት ያላቸውን ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
- ሎት አንድ :- የእንጨት ግብዓቶችን
- በሎት ሁለት : የፈርኒቸር መገጣጠሚያ እና የማጠናቀቂያ እቃዎች
- ሎት ሶስት : የኮላ እና ልዩ ልዩ ቀለሞች ሲሆኑ በዘርፉ ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ የተጋበዙ ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፤ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ፣ የተእ.ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ናሙና ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን ::
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለሎት አንድ 70,000 (ሰባ ሺ ብር) ለሎት ሁለት 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር) እና ለሎት ሶስት 50,000(ሃምሳ ሺ ብር) በሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ነሀሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8.00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8.00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግዴታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ Tel. 0116 -46-34 81 መረጃ ማግኘት ይላሉ ::
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ አና ማከፋፈያ ድርጅት