የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት
የእንጨት ግብዓቶች ግዥ በሀገር አቀፍ
ግልጽ ጨረታ ቁጥ.ት.መ.መ.ማ.ድ/ NCB/31/2012
ድርጅታችን ለፈርኒቸር ምርት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ የእንጨት ግብዓቶችን ለመግዛት ብቃት ያላቸውን አምራቾች እና አከፋፋይ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ ብቃት ያላቸውን አምራች እና አከፋፋይ በጨረታው እንዲሳተፉ የተጋበዙ ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ የተፈታ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፤ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ናሙና ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን ::
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ! ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችላሉ፡፡ –
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 70,000.00 (ሰባ ሺ ብር) በሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሐምሌ 07 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግዴታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም ከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- Tel. /0116 -46-34 81 መረጃ ማግኘት ይችላሉ ::
የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ አና ማከፋፈያ ድርጅት