ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር ገ/ኢ/ል/መምሪያ የታ/ጋ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በስሩ አገልግሎት ለሚሰጣቸው በወረዳው ውስጥ የሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በመደበኛ በጀት
- 1ኛ. የጽ/መሳሪያ
- 2ኛ. ባለ አራት እግር ተሽከርካሪ ጎማ ግዥ እንዲፈጸምላቸው በጠየቁት መሠረት ከተጫራቾች መካከል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስቀረብ ይፈልጋል::
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ናምበር/ ያላቸው
- የሞሉት ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የአቅርቦት ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአቅርቦት አይነት 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው:: ይህም ገንዘብ አሸናፊ ከሆኑ ከውል ማስከበሪያ ጋር ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል:: ተሸናፊ ከሆኑ ደግሞ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳብ በአንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች የድርጅቱን ክብ ማህተም በመምታትና በጥንቃቄ በማሸግ ታ/ጋ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለ ጀምሮ በሚቆይ የአቅርቦት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል:: በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል:: ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙም የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናል::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት /በሎት/ በመሆኑ የተጠየቁትን ዝርዝር አካተው መሙላት አለባቸው::
- መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ታ/ጋ/ወ/ግ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 268 02 18 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
ታች ጋይንት ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት