የግዢ ጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር 01/2013
የቱሉቦሎ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ ለሥልጠና የሚውሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን፣
- የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣
- የጸጉርና ውበት ዕቃዎችን፣
- የጽዳት ዕቃዎችን፣
- ብትን የደንብ ልብሶችን፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣
- የግንባታ መሳሪያዎችን፣
- የልብስ ስፌት ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎችን፣
- የፈርኒቸር መለዋወጫ ዕቃዎችን፣
- የመካኒክስ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች:
- የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No) እና VAT ተመዝጋቢ ከሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የዕቃዎችን፣ ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በደ/ምዕ/ሸዋ በበቾ ወረዳ ቱሉ ቦሎ ቴ/ሙ/ስ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 3 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7000 (ሰባት ሺህ ብር ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው
- የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል ::
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸው ቦታ ይከፈታል፡፡
- አስራ አንደኛው ቀን ዝግ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- አሸናፊው አሸናፊነቱ ከታወቀ ቀን ጀምሮ እስከ 10 ባሉት ቀናቶች በበቾ ወረዳ ቱሉቦሎ ቴ/መ/ስ ኮሌጅ ቱሉ ቦሎ ከተማ ከአ.አ 80 ኪሎ ሜትር በጅማ መንገድ ላይ በራሳቸው መጓጓዣ ዕቃዎችን አቅርበው ማስረከብ አለባቸው ::
- አሸናፊው በጨረታው መሰረት ዕቃዎችን በመሉ ሲያስረክብ ክፍያው ወዲያውኑ ይፈጸምለታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ :ስልክ ቁጥር 0113420166 /0920671074
የቱሉቦሎ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ
ቱሉ ቦሎ