የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 0000/2013
በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ በ2013 ዓ.ም በጀት አመት ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት እቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ፤
- ሎት 1.የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
- ሎት 2 የደንብ ልብስ ማሰፊያ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
- ሎት 3.አላቂ የቢሮ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
- ሎት 4. የተለያዩ የህትመት ውጤቶች— የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000.00
- ሎት 5 መድሐኒት የህክምና መገልገያ መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00
- ሎት 6 ሌሎች አላቂ የጽዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000.00
- ሎት 7የተለያዩ መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200.00
- ሎት 8.ፕላንት ማሽነሪ እና መሳሪያ መግዣ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000.00
- ሎት9.ህንጻ፤ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች መግዣ——– የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00
- ሎት10.ለሚንስትሪሚንግ እና ስልጠና አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1000.00
- ሎት11. ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳት እና ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000.00 ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፤
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፤ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ/ማቅረብ ላለባቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የስራ ቀናት በተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ በተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለሎት 1፤ ለሎት3፣ ለሎት6፣ ለሎት7 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ሎት 8 እና ሎት 9 ለተወዳደሩበት እቃ መስሪያ ቤቱ ባለበት ተቋም በሚልካቸው ባለሙያዎች የሚታይ ይሆናል፡፡ ለሎት 4 እና ሎት 5 መስሪያ ቤቱ ናሙና የሚያሳይ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎችና አገልግሎቶች ለእያንዳንዱ ከቫት ውጭ እና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊ ተጫራቶች ያሸነፉባቸውን እቃዎችና አገልግሎቶች በራሳቸው ትራንስፖርት ጤና ጣቢያችን ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ፤በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የተ/ክ/ሃ ጤና ጣቢያ
ስልክ ቁጥር 0115510957 ወይም 0115576978
(ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተክለሃይማኖት ቅርንጫፍ ወረድ ብሎ ጎላ ፓርክ አጠገብ)
በልደታ ክ/ከተማ ጤና መምሪያ
የተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ