የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2. ቋሚ እቃ፣
- ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ እቃ፣
- ሎት 4 ህንጻ መሳሪያ፣
- ሎት 5. ፈርኒቸር፣
- ሎት 6. ደንብ ልብስ፣
- ሎት 7. የተለያዩ ቆዳ ጫማዎች፣
- ሎት 8. ህትመት፣
- ሎት 9. የፅዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 10. የሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃዎች፣
- ሎት 11. የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣
- ሎት 12. የስፖርት ትጥቆችን በግልጽ ጨረታ በመደበኛ በጀት አወዳደሮ መግዛ ይፈልጋል።
ሰለሆነም:-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያለው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ትመዝጋቢ የሆነ፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ጎላ ብለው መነበብ መቻል አለባቸው፡፡
- ጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ ሙግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 15% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዋናናቅጅ ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ተሁለደሬ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ከ1/2/2013 ዓ.ም እስከ 16/2/2013 ዓም 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው 16/2/2013 ዓም 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል (ባያገኙም ይከፈታል)፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታ በቀጣይ የስራ ቀን የመከፈቻ ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት (በድምር ዋጋ ነው፡፡ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃው ዋጋ ሰሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች መ/ቤቱ በጠየቀው በእስፔስፊኬሽን መሠረት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተጋነነ ከሆነ ጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ሁሉም የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸው የተጠበቀ መሆን አለበት፡፡ አሸናፊው ድርጅት እቃዎቹን ተሁለደሬ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በራሱ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን በየንብረት ክፍሉ ድረስ አስረከቦ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወስዳል፡፡
- ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሞከረ ተጫራች የጨረታው ውጭ ሆኖ ለወደፊትም በመንግሥት ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- በጽ/ቤት መሳሪያ ሰነድ ተል 5፣ 48፣49፣ 50፣61፣ 62 ፥ 63፣64 ፤65/66፣69፣ 70.እና 71 የተዘረዘሩትን እቃዎችን በግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ ከሰነዱ ጋር በተቀመጠው ናሙና እናተመሳሳይ እቃዎችን በተቀመጡ ሳምፕሎች መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በደንብ ልብስ ሰነድ ተ.ቁ 1 እና በቆዳ ጫማዎች ሰነድ ከተቁ 1 -8 የተዘረዘሩትን እቃዎችን አሸናፊ ተጫራቾች ማቅረብ የሚችሉትን ጫማ ሳምፕል ለእያንዳንዱ የጫማ አይነት ቢያንስ 2 ናሙናዎችን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በኤሌከትሮንከስ ሰነድ ከተ.ቁ 4-7 የተዘረዘሩትን እቃዎችን በግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ ከሰነዱ ጋር በተያያዝው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 822 90 06 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ
ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት