ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ትም/ቢሮ የቦንጋ መም/ትም ኮሌጅ በ2013 ዓ.ም በጀት ዘመን ለኮሌጁ ትም/ት ስራ አገልግሎት የሚሰጡ፡–
- ጽህፈት መሳሪያዎች ፤
- የጽዳት ዕቃዎች ፤
- የህንጻና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፤
- የፕሪንተር ቀለሞች፤
- የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ፦
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያላቸው በተሠማሩበት የንግድ ዘርፍ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ የሚያቀርቡ፤ በግብር ከፋይነት የተመዘገቡና መለያ ቁጥር ያላቸው ድርጅቶች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር /በመከፈል ከኮሌጁ ግዥ/ንብ/አስ/ ደጋፊ የስራ ሂደት በመውሰድና ዋጋ በመሙላት ኮሌጁ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይችላሉ ፤
- ተጫራቾች የዕቃ ዋጋቸውን ከሞሉ በኋላ ለጨረታው ማስከበሪያ የጨረታውን ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ቦንጋ መም/ትም/ኮሌጅ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፍ የስራ ሂደት ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 15 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በዕለቱ ከ11:00 የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፤ በ16ኛው ቀን 2:30 የጨረታ ሳጥን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል ፤ 16ኛው ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። በጨረታ ሳጥን አከፋፈት ወቅት/ሥነ–ስርዓት ላይ ተጫራቾች አለመቅረብ የጨረታው አከፋፈት አያስተጓጉልም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የጨረታ መመሪያ አብሮ መያያዙን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፤፤
- ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ – በስልክ ቁጥራችን 0478991211 ወይም 0478319010 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ፋክስ ቁጥር 0473310228/0473310864
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ት/ቢሮ
የቦንጋ መም/ትም/ኮሌጅ