የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ወ/ሮ ሙና ያሲን እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ፋይዝ አሊ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 31999 በ21/7/2009 ዓ/ም፣ በመ/ቁ 128262 27/6/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ቀበሌ 15 በካርታ ቁጥር ቦጨ/055/97 ወ/ሮ ዙሪያሽ ሁሴን ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋት 250 ካ/ሜ የሀራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,654,540 (አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሃምሳ አራት ሺ አምስት መቶ አርባ ብር) (ትራንዛክሽን) ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 12 ቀን 2013 በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቁ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ ኣዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል :: ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች የጨረታው አይካፈልም በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያዩሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች
የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት