የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ በድጋሚ የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
የቦሬ ባኮ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን ኃ/የተ/ለ2013/14 የምርት ዘመን የሚውል “NPsB እና UREA” የአፈር ማዳበሪያ ከቡራዩ / ታጠቅ/ በምዕራብ ሸዋ ዞን በቦሬ ባኮ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን ሥር ላሉት መሠረታዊ የሕ/ሥራ ማኅበራት ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ሳይ ስመሳተፍ የምትፈልጉ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር (አ/ማ) የተመዘገባችሁበትን ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ አንንሾች የማንንዣ ታሪፋችሁን በማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መሠረት በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ/ በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ::
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው:-
- የ2013 ዓ.ም የታደሰ የሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ::
- የማጓጓዣ ታሪፍን በኩንታል እና በኪሎ ሜትር መስጠት አለባቸው፡፡
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም::
- ተጫራቾች ያላቸውን የመኪና ብዛት እና የመጫን አቅም ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማስረጃ ማቅረብ አለበት::
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አሥር /10%/ CPO ለመጫረት ካቀረበው የማዳበሪያ መጠን ጋር አጣጥሞ ማቅረብ አለበት፡፡ የጨረታው ማጣራት እንዳበቃ ለተሸናፊዎች ሲመለስላቸው ለአሸናፊዎች ግን ከመልካም የሥራ አፈፃፀም ላይ ይታሰብላቸዋል፡፡
- የማራገፊያ ጣቢያዎቹን እና የማዳበሪያውን ብዛት የሚገልጽ ሠነድ ባኮ ከተማ ከዩኒዬኑ ቢሮ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ በ5፡00 ሰዓት በዩኒዬኑ ቢሮ ይከፈታል:: 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በጨረታ መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅቱ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኘም በተገኙት ፊት ጨረታው ይከፈታል::
- በተቀራራቢ ጣቢያዎች ላይ የተጋነነ የዋጋ ልዩነቶችን ለማስታረቅ ሲባል ዩኒዬኑ የራሱን አማራጭ የመውሰድ መብት ይኖረዋል፡፡
- ዩኒዬኑ በትራንስፖርት ጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ሽዋ ዞን የቦሬ ባኮ ኃ/የተ/የገበሬዎች ሕ/ሥራ ዩኒዩን ስልክ ቁጥር፡– 09 42
94 10 11 /09 20 42 34 06 /09 17 72 39 12/ 0576651374
የቦሬ ባኮ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒዬን /ኃ/የተ/