የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2013
የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለ2013 በጀት አመት ለአንደኛ ዙር ግዥ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ
- ሎት 1 ቋሚ እቃዎች ፤
- ሎት 2 አላቂ እቃዎች
- ሎት 3 የእንስሳት መዳኒት እና የግብርና ዘር ዕቃዎች ፣
- ሎት 4 ደንብ ልብስ ፧
- ሎት 5 የስፖርት እቃዎች ፤
- ሎት 6 የመኪና ጎማ ፤
- ሎት 7 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 8 የትራንስፖርት አገልግሎት
- ሎት 9 መስተንግዶ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ፡
- በዘርፉ የተሰማራችሁ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና ቲን ነምበር
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ
- ቫት ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፡
- የጨረታ ማከበሪያ ብር በእያንዳንዱ ሎት 3000.00/ሶስት ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /CPO በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% በጥሬ ገንዘብ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም /CPO/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በo/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በቦሌ ክ/ከ ወ2 ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት አሮጌው 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2 የጨረታ ሰነድ በመግዛት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ብር በእያንዳንዱ ሎት 100 ብር/አንድ መቶ ብር /በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው 10ኛው ቀን ልክ 11፡00 ሰዓት ይዘጋና 11ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- 11ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታው ሰነድ መሉ በሙሉ በታሸገ ፖስታና ዋና ቅጅ ተብለው ስልጣን ባለው አካል መፈረም እና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት::
- ተጫራቾች በንግድ ፈቃዱ ላይ ያለውን የስራ መስኩን ከፊትም ከጀርባም ኮፒ ማድረገዎትን አይዘንጉ፡፡
- ተጫራቾች ናሙና በእቃ ወይም በፎቶ የተደገፈ ማስረጃ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ከፊትም ከጀርባም ኮፒ ማድረግ፡፡
- አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 12 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ልዩ ቦታው ቦሌ ቡልቡላከሳሪስ አቦ 3 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ /ከቦሌ ሚካኤል 4 ኪሎ ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
- ለበለጠ መረጃ ስልክ 011 471 46 73/988
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት