የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ቦሌ/ክ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት 001/2013
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግቢዎች ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
- ሎት አንድ:- የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- ሎት ሁለት:- የፅዳት ዕቃዎች፣
- ሎት ሦስት: ልዩ ልዩ የቋሚ አላቂ እቃዎች፣
- ሎት አራት:- የተለያዩ የደንብ ልብስ፣
- ሎት አምስት፡- የተለያዩ የህትመት ስራዎች፣
- ሎት ስድስት:- የቋሚ ዕቃዎች፣
- ሎት ሰባት፡- የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች እና የፕሪንተርና ፎቶ ኮፒ ማሽን ሰርቪስና መለዋወጫ ዕቃ አቅርቦት ግዥ ለ1 ዓመት የሚቆይ
- ሎት ስምንት፡- የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ለዓመት የሚቆይ 3000 እሽግ ግማሽ ሊትር ውሃ፣
- ሎት ዘጠኝ፡- የተለያዩ የመኪና ዲኮሬሽን ዕቃዎችና እጥበት ስራ፣
- ሎት አስር፡- የተለያዩ የፓርቲሽን ስራዎች፣
- ሎት አስራ አንድ፡- የቢሮ ምንጣፍና መጋረጃ ግዥ፣
- ሎት አስራ ሁለት፡- የድንኳንና ጀነሬተር ኪራይ አገልግሎት ግዥ ለዓመት የሚቆይ ግዥዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል::
- ከሚወዳደሩበት ዕቃ ወይንም አገልግሎት ግዥ ጋር ለመወዳደር የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃዎችን(ክሊራንስ) ከግብር አስገቢው መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ::
- በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት ግዥ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርቡ የማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(Tin Number) ሰርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ
- የአገር ውስጥ የድጋፍ እቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት (በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት) የተደራጁ መሆኑን እና ከአይራጃቸው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት አንድ 3000,00ብር/ሶስት ሺህ ብር/ለሉት ሁለት ሶስት እና፤ አራት 1000,00 ብር/ አንድ ሺህ ብር/ለሎት አምስት 2000.00ብር /ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት ስድስት 3000.00ብር/ሶስት ሺህ ብር/ ከዚህበታች የተዘረዘሩት ለሎት ሰባት፤ ስምንት፣ ዘጠኝ፣ አስር፣ አስራ አንድ እና አስራ ሁለት በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ 2% ለእንዳንዳቸው ሎቶች በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። CPO መሠራት ያለበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሚል አድራሻ መሆን ይኖርበታል::
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉትo ተከታታይ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6:30 ሰዓት ጨምሮ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መክፈቻው ቀን ድረስ አንበሳ ጋራዥ በስተጀርባ ከሚገኘው የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ከግዥ ቡድን አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 405 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ: የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያጠቃለለ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባችሁ::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋበጥንቃቄ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይገባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በግዥ ቡድን ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል እያንዳንዱ ተጫራች ለጨረታ መወዳደር በሚቀርብበት ወቅት ኦርጅናል እና ኮፒ የዋጋ ማቅረቢያ /ዝርዝር/በተለያየ ፖስታ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ኮፒ እና ኦርጅናል ተለይቶ በፖስታው ውጫዊ ገጽ መጻፍ አለበት፡፡
- ሰነዱን በሚመልስበት ወቅት ስልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃ መያያዝ አለበት፡፡
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም
- የጨረታው አሸናፊ የአሸናፊነት ደብዳቤ እንደደረሰው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር ፐርሰንት) CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል::
- ጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ናሙናዎችንም ለንብረት አስተዳደር ክፍል ማስረከብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ጀምሮ ለ90 ቀናት መቆየት አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስልክ ቁጥር፡- 0116-39-42-35
በአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
የቦሌ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
አዲስ አበባ