የጨረታ ማስታወቂያ
የቤ/ጉ/ክ/ኤች አይ ቪ በደማቸው ያለ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ህብረት የድርጅቱንና የ4 አባል ድርጅቶች (ተስፋ ብልጭታ ኤች አይቪ በደማቸው ያለ ማህበር 3 አቃፊ፤ ፍሬህይወት ኤች አይ ቪ በደማቸው ያለ ማህበር 2 አቃፊ፤ ተስፋብርሃን ኤች አይ ቪ በደማቸው ያለ ማህበር 2 አቃፊና እድገት በህብረት ኤች አይ ቪ በደማቸው ያለ ማህበር አንድ አቃፊ) የ2020 በጀት ሂሳብ ሰነድ የጥምረቱ 2 አቃፊ በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቶችን ይጋብዛል፡፡
በመሆኑም፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና በኢፕሳስ ፕሮግራም ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- በዓመቱ መጀመሪያ ወር መጀመሪያ ላይ ኦዲት ማድረግ የሚችል
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማረጋገጫ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ታትሞ ከወጣበት ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እያንዳንዱን ዋጋ በመግለጽ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 139 ቤ/ጉ/ክ/ አሶሳ ወይም email አድራሻ nbgpt2013@gmail.com መላክ ይችላሉ፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ የድርጅቱን ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር +251-577 751517/1983/ 0911-931891 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቤ/ጉ/ክ/ኤች አይ ቪ በደማቸው ያለ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ህብረት