የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2013
የቤ/ጉ/ክ/መ/አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2013 በጀት ዓመት ለሆ/ሉ አገልግሎት የሚውሉ
- መድሃኒቶች ፤ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎችና የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች እና
- በረኪና ኦሞ ፤
- የመኪና ጎማ ፤
- የደንብ ልብስ እና የወንድ እና የሴት ቆዳ ጫማ ፤
- ሙሉ ካፖርት ፣ የተዘጋጀ ሸሚዝ፣ ለድጋፍ ሰራተኞች የሚሰጥ ልብስ እና
- የተለያዩ ዕቃዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና የሴት ቦት ጫማ ፤ ለኦፕሬሽን ክፍል ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ በሙሉ፣
- በዘርፉ የአቅርቦት አገልግሎት ዝርዝር ላይ የተመዘገባችሁና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ።
- የዘመኑን ግብር የከፈላችሁና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ ሆኖ ኦርጅናሉንና ኮፒውን ማቅረብ የምትችሉ።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር/እና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላችሁ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚገልጽ ማረጋገጫ ማቅረብ የምትችሉ
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ካቀረቡት ዋጋ 3% ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የቤት ጋሪንቲ አንቀበልም።
- የመረካከቢያ ቦታ አሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ይሆናል።
- የአገልግሎት ጊዜ/Expired date / ለመድሃኒት ከአንድ ዓመት በላይ ላቦራቶሪ ከስድሰት ወር በላይ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ሰነድን ከኢፌዴሪ ጤና ቢሮ ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ።
- ጨረታው ለአስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ይውላል።
- ጨረታው ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ልክ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ በግልጽ ይከፈታል። ቀኑ ቅዳሜ/እሁድ/ወይም በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን የሥራ ቀናት ጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል።
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርበት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
- ተጫራቹ አሸንፎ ውል በገባ በ15 ቀን ውስጥ የአሸነፈበትን ዕቃ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ከጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ተከታታይ የስራ ቀናት በፌደራል እና ጥበቃ ሚ/ር ቢሮ በመገኘት መግዛት ይችላል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን 10% በማስያዝ ባሸናፊነት በ7 ቀናት ውስጥ ባይገባ ለጨረታ ያስያዘው 3% ለመንግሥት ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
- ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ–ሥርዓት ላይ ባይገኙ የጨረታውን ሂደት እያስተጓጉልም።
ለበለጠ መረጃ በስልክ 0909449421/0577751811
በቤ/ጉ/ክ/መንግሥት ጤና/ጥ/ቢሮ የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል