የጨረታ ማስታወቂያ
የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስራ አመራር ተቋም ለተቋሙ ለ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
በዚሁ መሰረት ለመወዳደር የምትፈልጉ
- ሎት 1 (አንድ ) ለሰልጣኞች የምግብ ዝግጅት የሚውል የምግብ ጥሬ ዕቃዎች (እህል)፣
- ሎት 2 (ሁለት)ለሰልጣኞች የምግብ ዝግጅት የሚውል የምግብ ጥሬ ዕቃ (የባልትና ዕቃዎች) ፣
- ሎት 3/ሶስት) ለሰልጣኞች የምግብ ዝግጅት የሚውል የምግብ ጥሬ ዕቃዎች አትክልትና ስራስር፣
- ሎት 4(አራት) ለሰልጣኞች የምግብ ዝግጅት የሚውል የምግብ ጥሬ ዕቃዎች የበሬ ስጋ (ለሙስሊም እና ለክርሲቲያን) ፣
- ሎት 5(አምስት) ለሰልጣኞች ምግብ አገልግሎት የሚውል የተጋገረ ዳቦ፣
- ሎት6(ስድስት) ለተቋሙ ሰልጣኞች የሚውል ለስላሳ መጠጦችና የታሸገ ውሃ ፣
- ሎት7(ሰባት) ለተቋሙ ሰልጣኞች ምግብ ዝግጅት የሚውል የማገዶ እንጨት ፣
- ሎት 8 (ስምንት) ለተቋሙ ሰልጣኞች ምግብ ዝግጅት የሚውል የምግብ ቤት ዕቃዎች፣
- ሎት 9 ( ዘጠኝ) ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- ሎት 10(አስር) ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል ሌሎች የቢሮ አላቂ ዕቃዎች፣
- ሎት 11(አስራ አንድ) ለተቋሙ ሰራተኞች የስራ ልብስ (ደንብ ልብስ)፣
- ሎት 12(አስራ ሁለት) ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ሎት 13(አስራ ሶስት) ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል ህትመት ስራ፣
- ሎት 14 (አስራ አራት) ለሁለገብ አገልግሎት የሚውል የውሃና የኤሌክትሪክ መለዋወጫ (ህንጻ መሳሪያ)፣
- ሎት 15 /አስራ አምስት/ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል ቋሚ ዕቃ
- ሎት 16 (አስራ ስድስት) የተሸከርካሪ ጎማ ፣ሲሆኑ
በተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመሳተፍ የምትፈልጉ
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባብነት ያለው በዘመኑ ግብር የከፈሉበትና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 50(ሃምሳ ብር) በመክፈል ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ስራ አመራር ተቋም አሶሳ አምባ አምስት ከግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 12 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት (አየር ላይ ከዋለበት) ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ መግዛትና መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ሥማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው በመፈረምና ማህተም በማድረግ (በመምታት) ዋናው (ዋጋ የሞሉበት) እና 1 ፎቶ ኮፕ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ከላይ በተዘጋጀው ቢሮ ላይ በቀረበው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው 16ኛው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በቀጣይ የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ (bid bond) ወይም ሲፒኦ (cpo) 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) በጥሬ ወይም በቼክ በአድራሻችን ቤ/ጉ/ከ/መ/ ስራ አመራር ተቋም ስም ተሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ተቋማችን ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ሳይለወጡና ሳይነካኩ በትክክል በዚሁ ሰነድ ላይ ወይም በራሳቸው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ ቅሬታ ካላቸው ለቤ/ጉ/ክ/መ/ስራ አመራር ተቋም በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 0911536324/ 0912400901/ 0930419148/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቤ/ጉ/ከ/መ/ስራ አመራር ተቋም አሶሳ አምባ 5፣
የቤ/ጉ/ክ/መ/ የስራ አመራር ማሰልጠኛ ተቋም