Garment and Leather / Garments and Uniforms / Shoes and Other Leather Products / Sport Materials and Equipment / Textile

የቤ/ጉ/ክ/መ/ ሴቶች፤ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮና የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን የሠራተኞች የደንብ ልብስና የስፖርት ትጥቅ፤ ቁሳቁስና አልባሳትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮና አጣምሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2013

የቤ//// ሴቶች፤ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮና የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ደጋፊ ዳይሬክቶሬቶችን አብሮ በፑል አገልግሎት በጋራ ይጠቀማሉ፡፡ በመሆኑም 2013 በጀት ዓመት አገልግሎት ለሚውል ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ

 • የሠራተኞች የደንብ ልብስና የስፖርት ትጥቅ፤ ቁሳቁስና አልባሳትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮና አጣምሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ለዚሁም ተጨራቾች ቀጥሎ በተመለከተው መስፈርት መሠረት ጨረታውን መግዛት ይችላሉ፡፡

ስለሆነም:-

1. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች:-

 1. ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድፍቃድ፤ የአቅራቢነት ሠርተፊኬት በክልል (በፌዴራል) ደረጃ የተመዘገቡበት፤ የተጫማሪ እሴት ታክስ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሠርተፊኬት ያለቸውና ከጨረታ ውድድር ያልታገዱ መሆን ይገባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታው ሠነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከሚገኘው የድሮ ብሔራዊ ሆቴል ህንፃ ላይ ከኢ.ፊ.. ስፖርት ኮሚሽን ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለሁለቱም ጨረታዎች ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ የኢትዮጵያ ብር) በመክፈል የጨረ ሠነድ መግዛት ይችላሉ::
 3. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶችንና የሚወዳደሩበትን የአንዱን ዕቃ ነጠላ ዋጋ ከቫት በፊትና በኋላ ያለውን በትክክል በማሰላት ለእያንዳንዱ ጨረታ በአንድ ኦርጅናል እና በሁለት ኮፒ ለያይተው በየውስጥ ገጾች እና በየፖስታው ጀርባ በድርጅቱ ህጋዊ ሥልጣን በላው አካል አጭሪ ፊርማና ከብ ማህተም በማሳረፍና ለስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ ወይም ለደንብ ልብስ መሆኑ በፖስታ ገጽ ውጭ በመጻፍ በሰም በታሸገው ኤንቨሎፕ አሽገው ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን ከጧቱ 4:30 ሰዓት ድረስ ማስገበት ይችላሉ ::
 4. ተወዳደሪ ድርጅቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ጨረታው በሚከፈትበት ቀን አንድ ቀን አስቀድመው ከጧቱ 230 – 10:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ይዘው በመቅረብ ማስረከብ አለባቸው፡፡ በባህርያቸው ክብደት ያላቸውን ዕቃዎች በየስቶካቸው ማሳየት ይችላሉ፡፡
 5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ ቀናት በሚቆጠር ቀናት በአስራ ስድስተኛው ቀን ከጧቱ ልክ 400 ሰዓት ላይ ታሽጎ ወደያው 4 30 ሰዓት ላይ ሁለቱም ጨረታዎች ይከፈታሉ፡፡ ዕለቱ የሥራ ላይ ካልዋለ በቀጣዩ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት የለውም።
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱ ጋር ተያይዞ የሚሰጣቸውን የተጫራቾች መመሪያን ማንበብና መተግበር አለበቸው።
 7. ተወዳዳሪዎች የጨረታ መስከበሪያ ለእያንዳን ጨረታ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ህጋዊ ሰውነት ካለው ባንክ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበቸው የሚዘጋጀው ሲፒኦ ለስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ስም ሲሆን ለደንብ ልብስ ደግሞ በቤንሻንኵል ክልል መንግስት ሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ስም ይሆናል። ውድድሩ እንዳበቃ ለተሸናፊ ድርጅቶች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
 8. አሸናፊ ድርጅቶች ባሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ 10% ለእያንዳንዱ ማስያዝ ይገባቸዋል :: አሸናፊ ድርጅቶች በመንግስት የግዥ መመሪያ መሠረት የሽያጭ አገልግሎት ዋጋን መክፈል ይገባቸዋል፡፡
 9. አሸናፊ ድርጅቶች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ 7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ውል መግባትና ውል ሰገቡ 15 ቀናት ውስጥ ዕቃዎቹን ሙሉ በሙሉ ማስረከብ አለባቸው
 10.  የመንግስት ግዥ አዋጅ እና መመሪያዎችና ግዴታቸውን በማይወጡት አሸናፊ ተጫራቾች ላይ ተፈፀሚ ይሆናል።
 11. አሸናፊ ድርጅቶች ባቀረቡትና ተቀባይነት ባገኘው ናሙናና አሸናፊ በሆኑባቸው ዕቃዎች ዓይነት ጥራትና መጠን ጠብቀው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 12. የክፍያ ሁኔታ በሚመለከት ቢሮው ዕቃዎቹን እንደተረከበ በትራንስፈር፤ በቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወዲያውኑ ለየድርጅቶቹ ክፍያን ይፈጽማል፡፡ በዚህ ጨረታ የቅድመ ክፍያ ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም። የማስረከቢያው ቦታ አ/ አበባ ሰሜን ሆቴል አካባቢ 3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት በሚገኘው ዮናታን ፔንስዮን ውስጥ ይሆናል፡፡
 13. በነጠላና በድምር ዋጋ መካከል ልዩነት ቢፈጠር የነጠላ ዋጋ ግንብ ይሆናል፡፡
 14. ስርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም ::
 15. ጨረታውን የሚፈርመው አካል ወኪሉ ከሆነ የውክልና ደብዳቤ መያያዝ አለበት::
 16. የጨረታ ዋጋ የጨረታው ውድድር ከተጠናቀቀ በኋላ ለስድስት ወር ጸንቶ ይቆያል፡፡
 17. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች በተሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
 18. ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 057  775 24 31  እና 09 17 17 20 42/09 11 53 35 79 መጠቀም ይችላሉ፡፡
 19. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የቤ//// ሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች

ጉዳይ ቢሮና የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን