የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ግንባታና ጥገና ጽ/ቤት በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሦስት ዞኖች ለመተከል ዞን፤ አሶሳ ዞን እና ካማሽ ዞን  ውስጥ በመንገድ ከፈታ እና በመንገድ ጥገና ሥራ ላይ ለማሰማራት ፣1 ሩሎ ለ1,000 ሰዓት፣ 1 ሎደር ለ1,000 ሰዓት፣ 5 ገልባጭ መኪና ለ130 ቀናት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 07/2012

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት መንገድ ግንባታና ጥገና ጽ/ቤት በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሦስት ዞኖች ለመተከል ዞን፤ አሶሳ ዞን እና ካማሽ ዞን  ውስጥ በመንገድ ከፈታ እና በመንገድ ጥገና ሥራ ላይ ለማሰማራት ፣ሩሎ ብዛት = 1 ሎደር ብዛት =1 ፣ገልባጭ መኪና ብዛት 5 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል። የሚሠሩበትን ሰዓት በተመለከተ አንዱን ሎደር ለ1000:00 (ለአንድ ሺ ሰዓት)፤ አንዱን ሩሎ፤ ለ1000፡00 (ለአንድ ሺ ሰዓት) አንዱን ገልባጭ መኪና ለ130 ቀናት ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የበጀት ዓመት ያሳደሱ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፣
  2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ድረ- ገጽ መግለጽ የሚችሉ
  3.  የሚያከራዩት መሣሪያዎች የራሳቸው ለመሆኑ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ ወይም አግባብ ባለው ባለሥልጣን መ/ቤት ሙሉ የሕግ ውክልና ማቅረብ የሚችሉ
  4. የድርጅታቸውን (የቢሯቸውን) አድራሻ ማሳየት የሚችሉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል አስፈላጊውን ማስረጃ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ ጋር በመያዝ አዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ቢሮ ቁጥር 2 ሁለት በመምጣት መግዛት የምትችሉ መሆኑን
  5. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት (አስራ አምስት) ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው (አስራ ስድስተኛ ቀንከቀኑ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው  በተገኙበት ይከፈታል::ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ህዝባዊ በዓላቶች እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እንዲከፈት ይደረጋል፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ አዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ቢሮ ቁጥር 2 የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7.  ተጫራቾች በጨረታው ላይ የሚወዳደሩበትን ማሽን ሊብሬ (የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር) ኮፒ ከጨረታ ዶክመንቱ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በተመለከተ ለአንዱ ሩሎ ብር 5,0000 / አምስት ሺህ ብር/ ለአንዱ ሎደር ብር 5,000.00 / አምስት ሺህ ብር/ ለአንዱ ገልባጭ መኪና ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብርበባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9.  ተጫራቾች ለተጫረቱበት የማሽን አይነት ተመጣጣኝ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው እንዲሁም ተመጣጣኝ ሲፒኦ ሳያስይዙ ዋጋ መሙላት አይቻልም፡፡ ተመጣጣኝ ያልሆነ ሲፒኦ አስይዘው ዋጋ ሞልተው ቢያቀርቡም በጨረታው ላይ እንዳልተሳተፉ ተደርጎ ውድቅ ይደረግባቸዋል፡፡
  10. መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0577752622/0326 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የቤ/ጉ/ክ/መ/መንገድ ግንባታ ጥገና ጽ/ቤት

አሶሳ