የጨረታ ማስታወቂያ
የቤ/ጉ/ክ/መ/ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ
- የ2013/14 ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ማጓጓዝና ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ 10/2013 ዓ.ም፤
- የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ (ፖለቲውን ቲውብ) ግዥ ጨረታ ቁጥር 14/2013ዓ.ም እና
- የተለያዩ የላብራቶሪ መገልገያ ቁሳቁሶች ግዥ ጨረታ ቁጥር 15/2013 ዓ.ም
የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተወዳዳሪዎች በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ዝርዝር ጨረታውን የያዘ ሠነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ) በመክፈል አ/አበባ ፌዴራል ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር በግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የውል ስምምነት ሲፈረም ለውል ማስከበሪያ ካቀረበው (ካሸነፈበት) ጠቅላላ ዋጋ 10% ያስይዛል፡፡
- በጨረታው ያልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ አሸናፊ እንደታወቀ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ሆኖ በ16ተኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ ነገር ግን ቅዳሜ፤ እሁድ እና የሕዝብ በዓል ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘጋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኣዲስ አበባ ፌዴራል ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር በግዥ/ንብ/አስ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ይሆናል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
መረጃ፡- ስልክ ቁጥር አቶ ሻምበል ኣፈታ 0913256787 አ/አ እና 0577752144 አሶሳ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት እና ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ