የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2012
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የመንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ለ2013 ዓም በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሶስት ዞኖች ለመተከል ዞን ኦሶሳ ዞን እና ካማሽ ዞን ውስጥ ለውስጥ በመንገድ ከፈታ እና በመንገድ ጥገና ሥራ ላይ ለማሰማራት፡-
ተ.ቁ |
የመሣሪያዎች አይነት |
ብዛት |
የስራው መለኪያ |
አመታዊ የሥራ መጠን /በሰዓትና በቀን/ |
1 |
ዶዘር |
4 |
ሰዓት |
1456 |
2 |
ግሬደር |
4 |
ሰዓት |
1456 |
3 |
ሩሎ |
3 |
ሰዓት |
1456 |
4 |
ሎደር |
3 |
ሰዓት |
1456 |
5 |
የውሃ ቦቴ |
2 |
ቀን |
182 |
6 |
የሰርቪስ መኪና ፒካፕ |
4 |
ቀን |
210 |
7 |
ገልባጭ መኪና |
10 |
ቀን |
182 |
ከላይ የተገለጹትን የመሳሪያዎችን በሰዓትና በቀን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል ።
በዚህም መሰርት፡–
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በጀት ዓመት ያሳደሱንና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ታክስ ከሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የምትችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዘጋቢ የሆኑ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላችሁ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገባች መሆናችሁ ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የሚያከራዩን መሳሪያዎች የራሳቸው ለመሆኑ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ ወይም አግባብ ባለው ሙሉ የህግ ውክልና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በማስኩ ስራ ላይ ለመሰማራታቸሁ ህጋዊ መስረጃ ማቅረብ የሚትችሉ ሁሉ ይህንን የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል አስፈላጊውን ማስረጃ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ ጋር በማድረግ አዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው በኢትዮጵያ የትራንሰፖርትና ዲዛይን ቁጥጥር ሱርቪዥኑ ኮርፖሪሽን ቢሮ ቁጥር 2 በአካል በመቅረብ መውስድ ይችላሉ።
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ15 ቀናት (አስራ አምስት) ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው (አስራ ስድስተኛ ቀን) ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሸጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተግኘበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የራ ቀን ካልሆነ ወይም ህዝባዊ በዓላቶች እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እንዲከፈት ይደረጋል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እንድ ኦርጂናልና ሁለት ኮፒ ዶክመንት ለየብቻ በማድረግና በማሸግ አዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው በኢትየጵያ የትራንስፖርትና ዲዛይን ቁጥጥር ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል ሰነዱን ይዞ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ተመግዛት ሲመጡ የሚያከራዩትን ማሸኖች የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር (ሊብሬ ) ኮፒውን እና የውክልና ደብዳቤ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ እና በእርሳስ የተሞላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም :: የሚቀርበው ዋጋ ከ15% ቫት በፊት ወይም ከቫት በኋላ ተብሎ በግልጽ ተጽፎ መቀመጥ አለበት ይህ ካልሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በተመለከተ ለእያንዳንዱ ማሽን የምትሞሉትን ዋጋ 0.01% በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ በመሆኑም ከባንክ ከተረጋገጠ CPO ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የስልክ ቁጥር 057 75 26 22
አሶሳ
የቤ/ጉ/ክ/መ/መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን