የማዕቀፍ ስምምነት ጨረታ ማስታወቂያ፣
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ለክልሉ 104 ግዥ ፈጻሚ የመንግሥት መ/ቤቶች ከ2013-2015 ዓ.ም ድረስ አገልግሎት ላይ የሚውሉ
- ምድብ 1 ስቴሽነሪ፤
- ምድብ 2 ፈርኒቸሮችን
- ምድብ 3 ኤሌክትሮኒክሶችን
- ምድብ 4 የተለያዩ ቀለሞች እና ድርሃም ኪቶችን በማዕቀፍ ስምምነት ግዥ በአገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአንድ ዓመት እስከ ሶስት ዓመት ሊቆይ የሚችል የማዕቀፍ ስምምነት ውል መፈራረም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ማንኛውም ተጫራች፡፡
- የማዕቀፍ ስምምነት ግዥ መለያ ቁጥር–የመ.ን.ግ.ማስ.አገ/የሀ.ው.ጨ/የዕ.አገ.ግዥ/15/2013 ነው፡፡
- በዘርፉ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TIN / ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት እና በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
- ለምድብ 1 ብር 100,000.00፤
- ለምድብ 2 ብር 120,000.00፣
- ለምድብ 3 150,000 እና
- ምድብ 4 30,000 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ከተሰጣቸው ባንኮች የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO)ወይም የባንክ ዋስትና ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ለሎች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ምድብ የማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ የኢትዮጵያ ብር በመክፈል ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 30 እና ከፌደራል የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 05 ውስጥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌደራል መንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ግቢ ቢሮ ቁጥር 05 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻው ቀን በበዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በጨረታ መክፈቻው ዕለት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ሂደቱን አያስተጓጉልም
ለበለጠ መረጃ 0577750437/0577752952
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
አሶሳ