የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2013
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት የክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት
- የመኪና ጐማዎች
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- የተለያዩ አላቂ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተምና መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
- በጨረታው የሚሳተፋ ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፋ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የታደሰ ንግድ ፈቃድ የተመዝጋቢነት /የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከዋናው ጋር የተመሳከረ ፎቶ ኮፒ ከሰነዶቹ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው የሚሳተፋ ማንኛውም ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከዋናው ጋር የተመሳከረ ፎቶ ኮፒ ቴክኒካሉንና ፋይናንሻሉን በተለያየ ሁለት ሁለት በሰም በታሸጉ ፖስታዎች ከሰነዳቸው ጋር አያይዞ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1.5% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከተገለፀው የጨረታ መነሻ ዋጋ ከ1.5% በታች የሚያቀርቡ ተጫራቾች በመጀመሪያ የቴክኒክ ግምገማ ውድቅ ይደረጋሉ፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች ድርጅቶች/ ከታወቁና ውል ከተፈረመ በኋላ ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት/CPO/ መልሰው መውሰድ ሲችሉ አሸናፊ ድርጅቶች ለውል ማስከበሪያ የሚውል አሸናፊ የሆኑባቸው ዋጋ 1ዐ% በማስያዝ መጀመሪያ ያስያዙትን /CPO/ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ሙሉ ሰነድ ከየካቲት 12 ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘው የኢፌዴሪ ግዥና ንብረት ማስወገድ ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ የሰነድ ሎት የማይመለስ ብር 100/ አንድ መቶ ብር / ከፍለው መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ለተከታታይ ለ15 የስራ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ ማስታወቂያው በወጣ በ15ኛው የስራ ቀን መጨረሻ ከቀኑ በ8፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0572750357/0911020435
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት
ክልል ም/ቤት ጽ/ቤት