Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Vehicle

የቤኒሻል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ሆሞሻ ወረዳ ገጠር መንገድ ሥራ ላይ ለማሰራት ዶዘር፣ ግሬደር ፣ሩሉ ፣ እስካቫተር፣ ሎደር፣ ገልባጭ መኪና፣ የውሃ ቦቴ ለመከራየት ይፈልጋል

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 1/2013

የቤኒሻል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ሆሞሻ ወረዳ ገጠር መንገድ ዴስከ በዲ.አር.ዲ.አይ.ፒ ኘሮጀከት/በስደተኞች ተጽዕኖ ምላሽ ልማት ፕሮጀከት በወረዳው ውስጥ በሚገኙ 3 የገጠር ቀበሌዎች ዳረሰጊያ፣ ሹላ፣ ጉሙ መስመር እና 2 የሆሞሻ የከተማ ቀበሌዎች አልገለዓ እና ቱመት ውስጥ በመንገድ ከፈታ እና በመንገድ ሥራ ላይ ለማሰማራት

 • ዶዘር……… ብዛት…..1 
 • ግሬደር…… ብዛት … 2 
 • ሩሉ………. ብዛ ……2 
 • እስካቫተር…ብዛት…. 2 
 • ሎደር……..ብዛት……1 
 • ገልባጭ መኪና ብዛት.6 እና
 • የውሃ ቦቴ ……ብዛት.3 ለመከራየት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2013 ዓም መሰረት አንዱን ዶዘር በሰዓት ሂሳብ ለ300,00 (ሶስት መቶ) ሰዓት አንዱን ግሬደር በሰዓት ሂሳብ ለ700፡00/ሰባት መቶ ሰዓት/፤ አንዱን ሩሎ በሰዓት ሂሳብ ለ600,00 (ስድስት መቶ) አንዱን እስካቫተር ሊ500/አምስት መቶ/ ሰዓት ሎደር 500፣00 (አምስት መቶ ሰዓት፤ አንዱን የውሃ ቦቴ 600፡00 ሰዓት፤ አንዱ ገልባጭ በሰነዱ ላይ በተቀመጠው መሰረት የአንድ ሜ.ኪ ውብ ብቻ በተቀመጠው መጠን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም፣ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳዳር የምትችሉ ይሆናል።
 1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ዓመት ያሳደሱ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፣
 2. የሚያከራዩን መሣሪያዎች የራሳቸው ከሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ በስማቸው ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ ወይም ማሽኑ የሌላ ከሆነ በፍትህ በኩል የተሰጠ ውክልና ሰነድ ከነ ሊብሬው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 3. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በይፋ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ሆሞሻ ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር D.B.02 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
 4. ጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ30 ቀናት (ሰላሳ) ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ31ኛው (ሰላሳ አንደኛው ቀን) ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቶች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆሞሻ ወ/ገን/ኢ/ል/ጽ/ቤት ይከፈታል።ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ህዝባዊ በዓላቶች እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን እንዲከፈት ይደረጋል።
 5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ስታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ሆሞሻ ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር D.R.02 ውስጥ ተዘጋጅቶ በተቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲያቀርቡ ለቴክኒካል 1 ኦርጅናልና 2 ኮፒ ሲሆን ለፋይናንሻል ደግሞ ኦሪጅናልና 2 ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት፤
 7. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ገንዘብ ለሁሉም ማሽን 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
 8. ማሽኑን በሆሞሻ ከተማ ድረስ ማስረከብ ይኖርበታል በተጨማሪም ከቀበሌ ወደ ቀበሌ ሲንቀሳቀስ የሎቤድ እና ማንኛውንም ወጭዎችን በአከራዩ ይሸፈናል።
 9. መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 10. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው የሁሉም ማሽኖች ተደምረው የቀረበው አነስተኛ ዋጋ ይሆናል።
 11. የኪራይ ዋጋ ነዳጅ እና ሰርቪስ እንዲሁም ቫትን ጨምሮ ነው።
 12. ተከራይ በእያንዳንዱ ባሸነፈበት ማሽኖች ውል በተገባበት የሥራ ሰዓት በተጨማሪ ለማሰራት አስፈላጊ ሁኖ ሊገኝ ውል በተገባበት ማሽን በሰዓትና በሜኪ ዋጋ ሳይቀየር ለፕሮጀክቱ ስትሪንግ ኮሚቴ ቀርቦ ውሳኔ ከተሰጠበት በኋላ ብቻ ይሆናል።
 13. ተጫራቾች መንገድ የሚሰራባቸውን ቦታዎች ቀድሞ ማየትና በመቃኘት ማሽነሪዎቻቸውን ማጓጓዝና ማንቀሳቀስ እንደሚችሉ ቦታዎችን ማየቱን ካሰሪው መስሪያ ቤት ማረጋገጫ ማቅረብ መቻል አለባቸው።
 14. አሸናፊው ተጫራች ውል ሲገባ የውል ማስከበሪያ የአሸነፈበትን 10 ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርበታል።
 • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር- 0978004187 ሆሞሻ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የቤ/ጉ/ክ/መ/ የሆሞሻ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት