የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ ሰለሞን አቻምየለህ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ አልማዝ ማማስ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር 92776 በ2/4/2013 ዓ.ም እና በመ/ቁ 65573 በ18/9/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የቤ.ቁ 566 ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኝ ይዞታ ስፋት 159.18 ካ.ሜ ቦታው 95 ዓመት የልማት ቀጠና (five rear Corridor development) ውስጥ የሚያርፍ መሆኑ ቤቱ አሁን ባለው (5 year strategic area addis ketem ) ፕላን ጥናት 1.67 ካ.ሜ መንገድ የሚነካ ሆኖ በአጎራባች በምስራቅ የቤ/ቁ 563-564-599 በምዕራብ መንገድ የቤ/ቁ 561 በሰሜን 565 ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 41,662.36 (አርባ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ሁለት ብር ከሰላሳ ስድስት ሳንቲም) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፈዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን ፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡ ቤቱን ለማየትና የበለጠ ለመረዳት በሚከተለው የስልክ አድራሻ ይደውሉ: 0909115431 / 0908888515
ቱመርካቶ.ኮም
(Apr 15, 2022)
ቱመርካቶ.ኮም
(Apr 15, 2022)
Bid closing date
May 19, 2022 10:30 AM
Bid opening date
May 19, 2022 10:30 AM
Published on
ቱመርካቶ.ኮም
(Apr 15, 2022)
ቱመርካቶ.ኮም
(Apr 15, 2022)
Bid document price
Bid bond
25%
Region
Addis Ababa
Sales, Disposals and Foreclosure
House and Building Foreclosure
Sales, Disposals and Foreclosure
House and Building Sale
FDRE Supreme Court Federal Courts Judgment Execution Directorate
ኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት