House and Building Foreclosure / House and Building Sale

የቤትና ቦታ ሽያጭ ጨረታ

የጨረታ ማስታወቂያ

የአፈፃፀም ከሣሽ አሚናት እንድሪስ የአፈፃፀም ተከሣሽ አህመድ ሲራጅ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ በአፈፃፀም ተከሣሽ ስም በፈንድቃ ከተማ ቀበሌ 01 በምስራቅ የባለው ቤት፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ የባለው ቤት መካከል ተዋስኖ የሚገኘውን በካርታ ቁጥር 717/06 በተከሣሽ ስም የተመዘገበው ቤትና ቦታ የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 665,547.00/ስድስት መቶ ስልሣ አምስት ሺህ አምስት መቶ አርባ ሰባት ብር / ሆኖ በጨረታ ህዳር 17 ቀነ 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ ጨረታ እንዲሸጥ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ትዕዛዝ በሰጠው መሰረት በፈንድቃ ከተማ ቀበሌ 01 አስ/ጽ/ቤት አንድ ተወካይ በመላክ እና የፈንድቃ ፖሊስ ጣቢያም አንድ ተወካይ ፖሊስ በመላክ ተወካዮች በተገኙበት የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሃራጅ ባይ ጨረታውን በበላይነት በመምራት ጨረታው ይካሄዳል፡: ስለሆነም በጨረታ መሣተፍ የሚፈልግ ሁሉ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ እና ለመሣተፊያ በባንክ ሲፒኦ ወይም አንድ አራተኛውን ገንዘብ በማስያዝ ተመዝግቦ መሣተፍ የሚችል ሲሆን አሸናፊው እንደታወቀ ያሸነፈበትን ከተቻለ ሙሉውን ካልተቻለ አንድ አራተኛውን ገንዘብ በፍ/ቤቱ ሞዴል 85 ማስያዝ የሚችል መሆኑን እንድታውቁት በአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት አዊ ተዘዋዋሪ ችሎት/ኮሶበር/ የሚያስችለው ተዘዋዋሪ ችሎት አዝዟል፡፡

የእንጅባራ ተዘዋዋሪ ችሎት