የ2ኛ ዙር መደበኛ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
-
የባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት፣ ቤቶች፣ ኮንስትራክሽንና አገልግሎት ጽ/ቤት የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት እና ባንክ ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት 6 (ስድስት) ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል ቦታ 1,100.95 (አንድ ሺ አንድ መቶ ነጥብ ዘጠና አምስት) ካ.ሜ ስፋት እና 2 (ሁለት) ለድርጅት/ ለንግድ የሚውል ቦታ 580.27 (አምስት መቶ ሰማንያ ነጥብ ሃያ ሰባት) ካሬ ሜትር ስፋት በጠቅላላ 1,681.22 (አንድ ሺ ስድስት መቶ ሰማንያ አንድ ነጥብ ሃያ ሁለት) ካሬ ሜትር ስፋት የተዘጋጀ 8 (ስምንት) ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል።
- በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከሰኔ 12/2010 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 250 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል በባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት፣ ቤቶች፣ ኮንስትራክሽንና አገልግሎት ጽ/ቤት የባቲ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ አዳራሽ ጎን LllDP ቢሮ በስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ መግዛት የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን።
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከሰኔ 12/2012 እስከ ሰኔ 25/2012 እስከ ቀኑ 11:00 ሰዓት ብቻ ይሆናል።
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርህ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል።
- ጨረታው የሚዘጋው ሰኔ 25/2012 ከቀኑ 11:00 ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው ሰኔ 26 /2012 ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በባቲ ከተማ ማዘጋጃ ኣዳራሽ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በአብክመ ከተማ ልማት ቢሮ እና በኢፌዴሪ ከተማ ልማት ቤቶች፣ ኮንስትራክን ሚኒስቴር ዌብ ሳይት ወይም በባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶች፣ ኮንስትራክንና አገልገሎት ጽ/ቤት የባቲ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ አዳራሽ ጎን UllDP ቢሮ በስራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ማግኘት ይቻላል።
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የባቲ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽንና አገልግሎት ጽ/ቤት