የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2013
የባሌ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በዞኑ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ
- የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ ቶነሮች ፤
- ቋሚና አላቂ ዕቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ ፈርኒቸሮች፣
- የግንባታ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች ፣
- የሠራተኞች ደንብ ልብሶች እና የልብስ ስፌት አገልግሎት እና
- ለስልጠና መስተንግዶ Refreshment/ የሚያገለግሉ ቀዝቃዛ እና ትኩስ መጠጦች እንዲሁም የተለያዩ ለቁርስ የሚያገለግሉ ምግቦችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት ዘርፍ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱና በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብይኖርባቸል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል ::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 15000.00 (አስራ አምስት ሺህ) ብር የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ሰነዶች ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ፤ እንዲሁም ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
- አቅራቢው ድርጅት ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ መ/ቤቱ ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርበታል::
- የደንብ ልብስ ናሙናዎችን ጨረታ ሰነድ ላይ የወጡትን በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / በባሌ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ስም በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000040165267 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማስገባት ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 15መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0226650225 ደውለው ይጠይቁ፡፡
የባሌ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት