የጨረታ ማስታወቂያ
የባሌ ሮቤ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኣ/ድርጅት
- ኤሌከትሮ መካኒካል እቃዎች ለጥቅል የውሃ ጉድጓዶች የሚውል የውሃ ፓንፕ (Submerseble pump)፣
- የቢሮ ዕቃዎች፣
- የፅህፈት እቃዎች፣
- የፅዳት ዕቃዎች፣
- የሳይክል ዕቃዎች፣
- ኤሌክትሮኒክሰ፣
- ፕላስቲክ ቧንቧዎች፣
- ለውሃ ዝርጋታ የሚውል Gl ቧንቧዎች ፣ Gl መገጣጠሚያዎች (fttings), የቧንቧ መፍቻና ጥርስ ማውጫዎች
- የመኪና ጎማዎች፣
- ክሎሪንና
- የሠራተኛ የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያማሱ ተጫራቾች አንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል በተሰማራበት ዘርፍ ህጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ንግድ ፋቃድ ያለው::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ከሮቤ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የማስታወቂያው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጨረታው ሰነድ በተጠቀሰው መሰረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በሙሉ የመጫኛና የማጓጓዣ ወጪውን በመሸፈን መስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው።
- የእቃዎቹን ዋጋ መስሪያ ቤቱ የሚከፈለው ተጫራቹ ለማቅረብ ውል የፈረመባቸውን እቃ ሙሉ በሙሉ በንብረት ክፍላችን ገቢ መሆናቸው ማስረጃ ሲቀርብ ነው።
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው በ3 ቀን ውስጥ መ/ቤት ቀርበው ውል መፈራረም አለባቸው።
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022 66527 57/022 665 18 70 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የባሌ ሮቤ ከተማ ውሃና ፍሳሽ
አ/ድርጅት