በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የባለሙያዎች ህብረት ለልማት(Professional Aliance for Development ) የተባለ የሲቪል ማህበረሰብ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲገለገልባቸው የነበሩትን ያገለገሉ መኪኖችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ በድጋሚ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ፡-
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን ከገዙ በኋላ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ በአዲስ አበባ ከተማ ወደ ጀሞ በሚወስደው መንገድ ከጀሞ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን ወደ ጀሞ መስመር 200ሜትር እንደተጓዙ በሚገኘው አፍሪካ ህንጻ ባለው ስፍራ በግልጽ ጨረታ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 9፡30 ሰዓት ድረስ ዘወትር ሰኞ ፧ እሮብ እና ዓርብ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን መኪና ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ /ፖስታ/ በአዲስ አበባ ከተማ ወደ ጀሞ በሚወስወደው መንገድ ከጀሞ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን ወደ ጀሞ መስመር 200ሜትር እንደተጓዙ በሚገኘው አፍሪካ ህንጻ ላይ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የድርጅቱ፡ ዋና መ/ቤት አስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /7/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ሰኞ ፤ እሮብ እና አርብ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በሶስት /3/ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በአምስት /5/ ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለደርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከድርጅቱ አስተዳደርና ፋይናንስ የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለተሽከርካሪዎቹ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /7/ ተከታታይ የስራ ቀናቶች ድረስ ዘወትር ሰኞ፣ እሮብ እና አርብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /7/ የስራቀናት ክፍት ሆኖ በ8ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 5፡00 ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙብት በአዲስ አበባ ከተማ ወደ ጀሞ ሰሚወስወደው መንገድ ከጀሞ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን ወደ ጀሞ መስመር 200ሜትር እንደተጓዙ በሚገኘው አፍሪካ ህንጻ ላይ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በመሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-0113698136/ 09890 15124/0911374503/0921898438 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የባለሙያዎች ህብረት ለልማት ባህል