Firewood / Foodstuff and Drinks / Products and Services / Wood and Wood Working

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤት መምሪያ ለ2013 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የሚሆን የምግብ እህል ፣የባልትና ውጤቶች ፣ አትክልትና የፋብሪካ ውጤቶች ፣ ድፍን ወፍራም እንጨት ለማገዶ የሚሆን፣ የፊኖ ዱቄት መግዛት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ማረሚያ ቤት መምሪያ ለ2013 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የሚሆን

 • ሎት 1 የምግብ እህል
 • ሎት 2 የባልትና ውጤቶች
 • ሎት 3 አትክልትና የፋብሪካ ውጤቶች
 • ሎት 4 ድፍን ወፍራም እንጨት ለማገዶ የሚሆን
 • ሎት 5 የፊኖ ዱቄት

ከላይ የተዘረዘሩትን አይነትና ብዛት ከጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የሚገኝ ሲሆን መወዳደር የሚፈልግ ከታች የተገለፁትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

 1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ከመንግስት ሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው ለመሆናቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 2. ከ200 ሺህ ብር በላይ ሽያጭ ለሚፈፅሙ አቅራቢዎች ቫት ከማይጠየቅባቸው የምግብ እህሎች ውጭ ባሉት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
 3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት ባህር ዳር ማረሚያ ቤት መምሪያ ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 100 በመክፈል ከመ/ቤቱ ገ/ያዥ ላይ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች በስራ ፈቃዳቸው መሰረት መቅረብ የሚገባቸውን የእህል አይነት ለይተው በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሣጥን ውስጥ ከጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
 5. ተጫራቾች ለመወዳደር ባቀረቡባቸው እቃዎች የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን 1 በመቶ በባንክ በተመሰከረለት/ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚያስዝ ሲሆን የባንክ ዋስትና ማስያዝ የማይቻል መሆኑን እናሣውቃለን፡፡ አሸናፊው ውል ሲይዝ የውል ማስከበሪያ በጨረታ ማስከበሪያ ላይ ገንዘብ በመጨመር የሚያስዝ ሆኖ ለተሸነፈ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ይሆናል፡፡
 6. ከ10 ሺህ ብር በላይ ለሆነ ሽያጭና ከ3 ሺህ ብር በላይ ለሆነ የአገልግሎት ሽያጭ ታክስ ከሚከፈለው ጠቅላላ ገንዘብ ላይ በመመሪያው መሰረት 2 በመቶ መክፈል ይኖርበታል፡፡
 7.  በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተረሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
 8.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በመለየትና በተለያየ ፖስታ በማሸግ ሰነዱ ላይ ፊርማ እና የድርጅታቸውን ማህተም ማሣረፍ አለባቸው፡፡
 9. የጨረታ አሸናፊዎች ውጤቱ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በማስያዝ ውል ይዘው ያሸነፋባቸውን እህሎች ባ/ዳር ማረሚያ ቤት መምሪያ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
 10. ጨረታው 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጐ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዛው ሰዓት ይከፈታል፡፡
 11. መምሪያው ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 320 3139፣ 0918082016፣0913366405 ደውለው ወይም በአካል ባ/ዳር ማረ/ቤት መምሪያ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት በመምጣት መጠየቅ ይቻላል፡፡

የባህር ዳር ከተማ አስ ተዳደር ማርሚያ ቤት መም ሪያ