ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
የባህርዳር ጨ/ጨ/አ/ማህበር የተሻለ ጥራት ያለው 10,500 ኩንታል የተዳመጠ ጥጥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ባህር ዳር ዋናው መ/ቤት ወይም አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ገዝታችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ መክፈቻው ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21(ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በሃያ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህር ዳር ዋናው መ/ቤት ግዥና አቅርቦት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ በጨረታ መክፈቻው ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻው ዕለት የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ፡ በስልክ ቁጥር ባህር ዳር፡0582200080/0582220661
አዲስ አበባ፡– 0115531381 /0115539742 ይደውሉ፡፡
የባሕር ዳር ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር