ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የቢቡኝ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በ2013 በጀት ዓመት ለሚገዙ እቃዎች ማለትም
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ፣
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣
- ሎት 3 የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች፣
- ሎት 4 ብትን ጨርቃ ጨርቅ፣
- ሎት 5 የተለያዩ ጫማዎች፣
- ሎት 6 የመኪና ጎማ ከነካላማደሪው፣
- ሎት 7 የውጭ ስሪት ወንበር፣
- ሎት 8 የቤት እና የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት 9 የጭነት አገልግሎት፣
- ሎት 10 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣
- ሎት 11 የተለያዩ ህትመቶች ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ለመጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በአዲሱ አዋጅ መሠረት የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣
- የግዥ መጠን ከብር 200 ሺህ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እቤት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የአሰሪው መስሪያ ቤትና የተጫራቹን ሙሉ ስምና አድራሻ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፍ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 ቀናት ውስጥ በጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/በጥሬ ገንዘብ/ በመሂ1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 ብር በመክፈል ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሣባቸውን ዋናውንና ቅጁን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በስራ ሰዓት ከ02/02/2013 ዓ/ም እስከ 16/02/2013 ዓ/ም 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በ16ኛው ቀን በ17/02/2013 ዓ/ም 3፡00 ይታሸጋል በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከላይ በሎት ከተዘረዘሩት እቃዎች ውስጥ መ/ቤቱ የእቃዎችን ናሙና በሚፈልግ ጊዜ እንዲያቀርቡ የሚጠየቁ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በሌላ በኩል አሸናፊው ድርጅት እቃዎችን በሙሉ በወረዳው ውስጥ ላሉ 4ቱም ፑሎች ሊያቀርብና በጥራት ኮሚቴ ተረጋግጦ ገቢ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ብሄራዊ የበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓትና ቀን ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈለጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በአካል በመገኘት /በስልክ ቁጥር 058 2540049/47 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቢቡኝ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት