የጨረታ ማስታወቂያ
የቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ የሠራተኞች የእሳት አደጋን ለመከላከል የሚጠቀሙ ትጥቆችን መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ አካላት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራቀንና ሰዓት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ በባንክ ሒሳብ ቁጥር 071 በቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ስም በማስገባት የገቢ ደረሰኙን ከቢሾፍቱ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን በመቁረጥ ከቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር የግዥና ንብረት የሥራ ሂደት 2ኛ ፎቅ አስፈላጊውን መረጃ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በመያዝ እስከ 10/9/2012 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bank guaranty) በመጫረቻ ሰነድ ላይ በሚጠየቀው መሰረት ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በመጫረቻ ሰነድ ላይ በሚጠየቀው መሰረት በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ በኤንቨሎፕ ላይ የተጫራቹን ስምና አድራሻ ሰነዱ ኦርጅናል ወይም ኮፒ መሆኑን በመጻፍ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር የግዥና ንብረት የሥራ ሂደት 2ኛ ፎቅ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትው በ10/9/2012 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ በ8፡30 ሰዓት በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር መሰብሰቢያ አድራሽ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፍልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 011 4 30 17 58 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ጽ/ቤት