የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2013 ዓ.ም
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በጉራጌ ዞን የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለ2013 የበጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- የጽህፈት መሳሪያዎች እና
- የጽዳት እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ተጫራቾች፦
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የቲን ነምበር ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000/አስር ሺህ ብር/ ብቻ በBID BOND ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዳቸው ጋር በተናጠል ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ ቴክኒካል መረጃዎችን በአንድ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማለትም 1 ኦርጅናል እና 2 ኮፒ በመለያየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ላይ ቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች / ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
- ይህ የጨረታ ዋጋ ለ45 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ /የህዝብ በዓል/ ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈትው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ብቻ በመክፈል ቡታጅራ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ን/አ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 01 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 046-145-67 77 ወይም በ046-115-06 07 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት