ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/በጌደኦ ዞን የቡሌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለአገልግሎት የሚውል
- ምድብ 1 የኤሌክትሮንክስ ዕቃዎች
- ምድብ 2 ሞተር ሳይክል
- ምድብ 3 የደንብ ልብስ በጣቃ
- ምድብ 4 ስቴሽነሪ
- ምድብ 5 ፈርኒቸር
- ምድብ 6 የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ለመግዛት ይፈልጋሉ፡፡
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ጋር፣
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ አግባቢነት ያለው ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው/ት፣
- የግብር ከፋይነት ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ሰርተፊኬት እና ቲን ነምበር ያለው /ት፣
- በአቅራቢያዎች ዝርዝር ላይ የተመተመዘገቡበት የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል /ት
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ማስረጃ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤቱ ማቅረብ የሚችል/ት
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከቡሌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 የማይመለስ 50 /ሃምሳ ብር/ በመከፈል ዘውትር በሥራ ሠዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስመሰከርያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ 5,000.00/አምስት ሺህ ብር/ በፖስታ በማሽግ ከኦርጅናል ሠነድ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
- ተጫራቾች የዕቃውን ነጠላ ዋጋ ከነቫቱ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው ፡፡ ይህ ካልሆነ የቀረበ ዋጋ ከነቫቱ እንደቀረበ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች የእቃውን ዝርዝር ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከጨረታ ሰነድ ጋር አባሪ አድርገው በተሰጠው ስፔሲፊኬሽን ላይ በመሙላት የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ ማሳረፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በሁለት ፖስታ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በሰም በማሸግ ከ1-4 የተዘረዘሩትን የህጋዊነት ማረጋገጫ መረጃዎችን አሟልተው በሁለቱም ፖስታ የሚያቅረብ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ተከታታይ ለ15ኛው ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽገው በ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን እሁድ እና ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ ሥራ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽገው በ8፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተወካዮች ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ይዘው መቅረብ አለባቸው :: ማስረጃ ካልያዙ መሳተፍ አይችሉም ።
- ተጫራቾች በዝርዝር አሽናፊ ከተገለጸበት እና ውል ካሳረፉበት ቀን ጀምሮ እስከ 03/3/2013 ዓ/ም ድረስ ያለምንም ዋጋ ለውጥ መ/ቤቱ በሚያቀርብለት ፍላጎት መሠረት ደረጃቸውና ጥራታቸውን በጠበቀ አኳኋን በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል፣
- አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች መ/ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አማልቶ እና በተፈለገው ጊዜ በመ/ቤቱ ጥራት ኮሚቴ ተረጋግጦ ካልተቀበለው ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት፡፡ ስለሆነም ሰመ/ቤቱ ጥራት ተረጋግጦ ገቢ ሲደረግና ሞዴል 19 ሲቆረጥ ብቻ ክፍያ ይፈፀማል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ ጨረታ ያሸነፉበትን የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር — 0910583598
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/በጌደኦ ዞን የቡሌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ዋና ጽ/ቤት