ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገ/ኢ/ት/ዋ/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በዋን ዋሽ በጀት ለወረዳው ው/መ/ኢ/ል/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል፡
- ሎት 1. የውሃ ዕቃ
- ሎት 2. የግንባታ ማቴሪያል ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው::
- ግዥ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30(ሰላሳ ብር) ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይቻላል፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማሰከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በበየዳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡ አሸናፊ የሚለየው በየሎት ወይም በጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከ2/4/2013 ዓ.ም እስከ 1/5/2013 ዓ.ም በበየዳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ ሣጥኑን በ2/5/2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈውን ንብረት በበየዳ ወረዳ በሚገኙ በግብርና ፑል ንብረት ክፍሎች ማስረከብ የሚችል እና ማውረጃ እና መጫኛ በተጫራቹ መሸፈን የሚችል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሰረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር ፡-0583272313 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት
በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገ/ኢ/ት/ዋ/ጽ/ቤት