ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገ/ኢ/ት/ዋ/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወ/ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- የስቴሽነሪ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ::
- ግዥ ከ200.000 /ሁለት መቶ ሺህ/ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተቁ ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30/ሰላሳ/ብር ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይቻላል፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.አ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ጠቅላላ–ዋጋውን -10% – የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሰ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ሳይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያገቡ የሚችል
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በበየዳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡ አሸናፊ የሚለየው በየሎት ወይም በጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች 10/02/2013 ዓ/ም እስከ 24/2/2013 ዓ/ም በበየዳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
- ጨረታ ሳጥኑን 25/02/2013 ዓ/ም 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ህጋዊ ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ያሽነፈውን ንብረት በበየዳ ወረዳ በሚገኙ በአራቱ ንብረት ክፍሎች ማስረከብ የሚችል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሰረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በኣካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 0583272313 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን
አስተዳደር የበየዳ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ዋ/ጽ/ቤት