ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገ/ኢ/ት/ዋ/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወ/ሴ/መ/ቤት የመኪና መለዋወጫ /ስፔር ፓርት ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- ግዥ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተቁ ከ1-4 የተቀሱትንና የሚመለታቸውን ማስረጃዎች በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይቻላል፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል፡፡
- አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በበየዳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ የሚለየው በየሎት ወይም በጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች 12/01/2013 ዓ.ም እስከ 26/01/2013 ዓ.ም በበየዳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑን 27/01/2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ሕጋዊ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈውን ንብረት በአሸነፈው መጋዘን ማስከረብ የሚል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሠረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 0583272313 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር ያበያዳ
ወረዳ የገ/ኢ/ት/ዋ/ጽ/ቤት