የበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት
ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር በስ/የአ.አቃ/ሽያጭ/ግጨ/05/2012
በኢፌዴሪ ስኳር ኮርፖሬሽን የበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በአማራ ክልል በአዊ ዞን በጃዊ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ፕሮጀክቱ ያገለገሉ እቃዎች
- ሎት 1 ቁርጥራጭ ብረታ ብረት፣
- ሎት 2. የተሽከርካሪና ማሽነሪ ጎማ፣
- ሎት 3. የተሸከርካሪና ማሽነሪ ባትሪ፤
- ሎት 4 አልጋ፣ ፍራሽና ትራስ፤
- ሎት 5. በርሚልና ጀሪካን፤
- ሎት 6 ባለ 50 ኪ/ግ ጆንያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በመስኩ ህጋዊ የዘመኑ ወይም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛቋንቋ ሲሆን ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ 50 /ሃምሳ ብር በጥሬ ገንዘብ በመከፈል በድርጅቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ባህር ዳር ከተማ ቅ/ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናቶች ማለትም ከo4/09/2012 ዓም እስከ 18/09/2012 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፣ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /CPO/ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ወይም ጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያው ሠነድ በሁለት ኮፒ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ሰነዶቹ ተለይተው በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በድርጅቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ባህር ዳር ከተማ ቅ/ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ማለትም 18/09/2012 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ባህር ዳር ከተማ ቅ/ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ያገለገሉ እቃዎችን ርክክብ የሚፈፀመው ጃዊ በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ንብረት ማከማቻ ክፍል/ መጋዘን/ ይሆናል፡፡
- ፕሮጀክቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 05823117 07 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኢፌዲሪ ስኳር ኮርፖሬሽን የበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት