ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የቆላድባ ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጂ በ2013 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚያስፈልጉትን
- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 2. የኮምፒተር እቃዎች
- ሎት 3. የጽዳት እቃዎች
- ሎት 4. የኮንስትራክሽን እቃዎች
- ሎት 5. የብረታ ብረት እቃዎች
- 6. የኤሌክትሪክሲቲ እቃዎች
- 7. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች
- 8. የግብርና እቃዎች
- 9. የጋርመንት እቃዎች
- 10. የደንብ ልብስ ብትን
ጨርቅ እና ቆዳ ጫማ የሴትና የወንድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት መወዳደር የምትችሉ
መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው ለመሆኑ ማረጋገጫ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና ከተራ ቁጥር 1-10 የሚመለከታቸውን ነጋዴዎች ወይም ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ንግድ ፈቃድ የእያንዳንዱ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያያዝው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚገዙት እቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም የሚጠይቁትን ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50.00/ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከቆላድባ ቴ/ሙ/ማ/ ኮሌጅ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመስሪያ ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ገቢ ተደርጎ ካርኒው ከሰነዱ ጋር ከሳጥኑ ውስጥ መግባት አለበት፡፡
- የጨረታው አሸናፊ መሆን የሚችለው በተጫረተበት ዘርፍ በነጠላ ዋጋቸው ዝቅተኛ ዋጋ የሞሉ መሆኑ ታውቆ በሰነዱ ጥቅል እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን በኃላ የውል ማስከበሪያ ካአሸነፈበት ከጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ ከተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዎል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቆላድባ ቴ/ሙ/ማ/ኮሉጅ የውስጥ የጨረታ ማስታወቄያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 5፡00 ታሽጎ 7፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቆላድባ/ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ ግዥ/ፋ/ን አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 5፡00 ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን እቃ መስሪያ ቤቱ ከሚፈለግበት ቦታ ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብ አለበት፡፡ በተጨማሪም የሚቀርቡ እቃዎችን በባለሙያ እያረጋገጥን የምንረከብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት፡፡ ሆኖም ስርዝ ድልዝ ካለው ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ ለጨረታ በቀረቡ እቃዎች መጠን 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ግዥ ክፍል ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583350550 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በዚህ ጨረታ ያልተገለፁ ጉዳዩች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
የቆላድባ ቴ/ሙ/ማ/ኮሉጅ