የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ፤
የቅ/ልደታ ለማርያም የጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ የ2011 እና 2012 ዓ.ም የሂሳብ ሪፖርት በውጪ ኦዲተር ለማስመርመር ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቅድስት ልደታ ቤተ–ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው በማኅደረ–ስብሐት ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 208 ማስረጃችሁን በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች:-
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፤
- የሙያ ማረጋገጫ ያለው፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውንና የዘመኑን ግብር መክፈሉን ማስረጃ የሚያቀርብ፤
- የወቅቱን ግብር የከፈለበት ማስረጃና የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችል፤
- ሥራውን ሰርቶ ለመጨረስ የሚፈጅበትን ጊዜና ዋጋ የሚያቀርብ፤ አድራሻ፡– ከባልቻ ሆስፒታል ፊት ለፌት ቅድስት ልደታ ቤተ–ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው በማኅደረ–ስብሐት የኮሌጁ ሕንፃ ውስጥ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 208
ስልክ ቁጥር፡– +251 11 515 7819/ 251911468123