የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት እና በስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የግዥ/ን/አስ/ጠ/አገልግሎት ደጋፊ የስራ ሂደት ለተለያዩ የስራ ክፍሎች የሚውል፡፡
- የደንብ ልብስ
- አላቂ የጽህፈት እቃዎች
- ልዩ ልዩ እቃዎች
- አላቂ የጽዳት እቃዎች
- ፈርኒቸር
- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ህትመት
- የመኪና ከመነዳሪ
- የመኪና ውስጥ እቃዎች
- የከባድና የቀላል የመኪና እጥበትና ተያያዥ
- የከባድና የቀላል መኪና ጥገና
- የከባድና የቀላል መኪና ጎማ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን ቲን ማቅረብ የሚችል፤ እና በአዲስ ኣበባ ከተማ አስተዳደር አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡00 በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት በግዥ/ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 1ኛ ደንብ ልብስ ብር 3000 2ኛ. አላቂ የጽህፈት እቃዎች ብር 5,000 3ኛ. ልዩ ልዩ እቃዎች 3,000 4ኛ አላቂ የጽዳት እቃዎች ብር 3,000 5ኛ. ፈርኒቸር ብር 3000 6ኛ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 10,000 7ኛ ህትመት ብር 3,000 8ኛ የመኪና ከመነዳሪ ብር 2,000 9ኛ የመኪና ውስጥ እቃዎች ብር 2,000
- 10 የከባድና ቀላል የመኪና እጥበትና ተያያዥ ብር 2,000 11ኛ የከባድና ቀላል መኪና ጥገና ብር 10,000 12ኛ. የከባድና የቀላል መኪና ጎማ ጥገና ብር 10,000 በባንክ በተመሰከረለት CPO /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው ::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛ ቀን ድረስ በቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃዎች ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት መቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ባሉበት ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ10ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት በሚገኘው አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- ለጨረታ ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለጨረታ የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
ስልክ ቁጥር 0115580040 ወይም 0118545712 መደወል ይችላሉ
አድራሻ ከእስጢፋኖስ ወደ 22 በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ አጠገብ ኣዲሱ ቢሮ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት የግዥ/ን/አጠ/አገ/ደ/የሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 30
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ጽ/ቤት