የሠርቪስ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር የቢ/ዕቃ/ 16 /2012
የቂርቆስ ቤቶች ልማት ኘሮጀክት ቅ/ጽ/ቤት ለሠራተኞች የሠርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ ኮድ 3 -ሚኒባስ ታክሲ ብዛት 2/ሁለት መኪና ከ12-15 ሰው የመጫን አቅም ያለው ነዳጅ፣ሹፌር፣ ለመኪናው የሚያስፈልጉ ወጪዎችን በራሱ ችሎ መስራት ለሚፈልግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው የሚወዳደሩ አቅራቢዎች፣ የሚያቀርቧቸው መኪኖች የቴክኒክ ብቃት ችግር የሌለባቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ማስረጃ፤ የባለቤትነት ሊብሬ መታወቂያ፣ ሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአንድ መኪና ብር 3,000.00 ብር /ሶሶት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ቼከ፣ ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ (ከቴክኒካል ሰነድ) ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በቢድ ቦንድ /የጨረታ ማስከበርያ/ ያልተደገፈ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዝርዝር መግለጫን የያዘ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ቦሌ አራብሳ 5 እየተገነቡ ካሉት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ ከሚገኘው ቢሮ የቂርቆስ ቤቶች ልማት ኘ/ቅ/ጽ/ቤት የክፍያና ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ፋይናንሻል ሰነድ) እና (ቴክኒካል ሰነድ ) ተብሎ በ2 በታሸገ ኤንቨሎኘ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ( ቅዳሜ እንደ አንድ የስራ ቀን ይቆጠራል) ዘወትር በስራ ሰዓት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በግዥ እቅድና ዝግጅት አፈፃፀም ደጋፊ የስራ ሂደት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የመኪኖች ቴክኒክ ፍተሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 9:00 ሰዓት ቅዳሜ ከሆነ እስከ 6፡00 ሰዓት እንዲሁም በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ይካሄዳል፡፡ በእለቱ ተገኝተው መኪናው ቴክኒካል ያላሳየ ተጫራች ያቀረበው ፋይናንሻል ፖስታ አይከፈትም፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0118-26-50-78 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ –
በአ/አ/ከ/አስ/ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የቂርቆስ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት