ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሰሜን ወሎ ዞን የሸደሆ መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለሸደሆ መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል
- የመድሃኒትና የህክምና መሣሪያዎች፣
- የጽዳት እቃ፣
- የጽህፈት መሣሪያ፣
- ደንብ ልብስ፣
- የውሃ ዕቃዎች፣
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- የኤሌክትሪክ እቃዎች፣
- የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣
- APTS የመድሃኒት መደርደሪያ እና ማስተናገጃ
- አልሙኒየም ስራ እና ማዋቀር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች/ግዴታዎች/ ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣
- ተጫራቾች ጥራት ያላቸው እቃዎች ማቅረብና ባቀረቡት እቃ ላይ ጥራት የሌላቸውን ቢያቀርቡ የመቀየር ግዴታ አለባቸው፡፡ የተገዙ እቃዎች ሚገጣጠሙ ከሆነ የመገጣጠሚያ ወጭ በራሣቸው ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዶች ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በስም በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የግዥ መጠኑን ከ50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ 1 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን ውስጥ ሰነዶች መቄት ወረዳ ሸድሆ መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ የማይመለስ ብር 30 በመክፈል መውሰድና ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚገባበት ጨረታው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 3፡30 ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በክልሉ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
- ሆስፒታሉ በጨረታ ሰነዱ የተዘረዘሩ እቃዎች 20 በመቶ የመቀነስና መጨመር መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ ለማቅረብ ውል በፍትህ መውሰድ ሚችል መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ መቄት ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግቢ ድረስ ዕቃው ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው፡፡
- ሆስፒታሉ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣፣
- ለአሸናፊዎች ያሸነፉትን ዕቃ ወይም መድሃኒት ቤቱ እንደሁኔታው አይቶ በሎት ወይም በተናጠል አሸናፊ ሊያደርገው ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር 033 211 0726/033 211 00 00 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሸደሆ መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል